ቀን፡-25/01/2017
ዓ.ም
የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
ለጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለ አክሲዮኖች በሙሉ !
የጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በ2550 ባለ አክሲዮኖች በብር
54,110,000 መነሻ ካፒታል በመያዝ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ፈቃድ ስለመስጠትና ስለመቆጣጠር በወጣው
አዋጅ ቁጥር 626/2001 መሰረት በ03/06/2022 እውቅና በማግኘት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ በመሆኑም 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ
እና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በሙሉ ዓለም የባሕል ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ
ያካሂዳል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጉባዔው እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ
2.
በነባር በባለአክሲዮኖች የተገዙ ተጨማሪ አክሲዮኖችን
መቀበልና ማጽደቅ፤
3.
በባለአክሲዮኖች የተደረገ የአክሲዮን ዝውውርን ማጽደቅ፤
4.
አድስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
5.
እስከ ጁን 30/2023 አመት ድረስ በነበረዉ ትርፍ (Retainied Earning) ላይ ተወያይቶ
መወሰን፤
6. የዳይሬክተሮች ሪፖርት ማዳመጥ፤
7. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና በሁለቱም ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
8. የ2023/24 በጀት ዓመት በተገኘው ትርፍ ክፍፍል ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
9. ተቋሙን ለሚቀጥሉት 3 ተከታታይ ዓመታት የሚመሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት
ምርጫ ማካሄድ፤
10. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ
ማጽደቅ
የአስቸኳይ (ድንገተኛ) ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
ማሳሰቢያ፡- በጉባዔው ስትመጡ የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንድትይዙ እና በጉባዔው መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከጉባዔው 3 ቀናት በፊት የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ባሕር ዳር ከተማ አጼ ሰርፀድንግል ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው በዋና መስሪያ ቤቱ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትወክሉ ያሳስባል፡፡
የዳይሬክተሮች
ቦርድ!!